Wed. Oct 9th, 2024

የመጀመሪያው ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ l ቪዛ ዳይሬክት l ቴሌብር ሬሚት l Virtual Visa Card #Ethiotelecom #telebirr #VISA #BOA

የመጀመሪያው ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ l ቪዛ ዳይሬክት l ቴሌብር ሬሚት l Virtual Visa Card  #Ethiotelecom #telebirr #VISA #BOA

ኩባንያችን ከቪዛ ጋር በመተባበር በሀገራችን የመጀመሪያውን የዋሌት ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ እንዲሁም ሀዋላን በእጅጉ የሚያዘምኑ ቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት የተሰኙ አገልግሎቶችን በይፋ አስጀመረ፡፡

የቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት ከ190 በላይ ሀገሮች የሚኖሩ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች በሀገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የቴሌብር ቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር በመጠቀም ገንዘብ ወደ ሀገርቤት በምቾት፣ በቅልጥፍና እና በቅናሽ መላክ ያስችላቸዋል፡፡

ደንበኞች በቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት ገንዘብ ለመቀበል በቅድሚያ የዘመነውን ቴሌብር ሱፐርአፕ በመጫን ከዚያም ለአገልግሎቱ በመመዝገብ ባለ16 አሀዝ የቨርቹዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የቴሌብር ሬሚት አገልግሎት ደግሞ ተጠቃሚዎች ከአሜሪካ፣ ካናዳ፣ እስራኤል፣ ሳኡዲአረቢያ፣ ዩናይትድ አረብኢምሬትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጣሊያን እና ስዊድን ለዚሁ አገልግሎት በኩባንያችን የበለጸገውን ዘመናዊ የቴሌብር ሬሚት መተግበሪያ በመጫን ገንዘብ ለቴሌብር ደንበኞች በቀጥታ መላክ ይችላሉ፡፡

የዘመነውን ቴሌብር ሱፐርአፕ በመጫን “VISA” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ለቨርቹዋል ቪዛ ካርድ እንዲያመለክቱ በደስታ እንጋብዝዎታለን!

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/fpgu4m ይጫኑ!

ለተጨማሪ፡ https://bit.ly/4fQbrFC ይጠቀሙ፡፡

#Ethiotelecom #telebirr #VISA #BOA #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia

Related Post